Circulation of random thoughts
Doro ManeQiya - ዶሮ ማáŠá‰‚á‹« ranks 2609 in Africa and 21 in Ethiopia. According to site visitors it ranks 4997, and 4997 according to page views:
According to blogroll links it ranks 2942 and 2853 according to the amount of links within Afrigator blog posts
እንካ ሰላምታ በምንትያ? በንቀት ምን አለ በንቀት? እማን ላይ ነው አንጃ የምታስፈጥሩት? እንካ ሰላምታ በምንትያ? በአክብርዎት ምን አለ በአክብርዎት? ጋሼ ወይስ ኢንጂነር፣ ምን ብዬ ልጥራዎት? እንካ ሰላምታ በምንትያ? በከፋኝ ወይ፣ በሞትኩት፣ ምን አለ በከፋኝ? ርእስ አትቀይር፤ ጋሼ ኢንጂነር በለኝ! እንካ ሰላምታ በምንትያ? በጤና
አከበርናቸው፤ ሰገድንላቸው፤ ፈራናቸው፤ አደነቅናቸው፤ ከፈጣሪም ሳንለያቸው። ነገሱብን፤ ገዙን፤ መሩን፤ አለፉ፤ ሌሎችም ተተኩ። እኛም ቆየን፤ አንዳንዴም ቆሰልን፤ አንዳንዴም ተከፋን፤ አንዳንዴም ተራብን፤ አንዳንዴም ሳያልፍልን፣ ጊዜው አለፈብን፤ ግን ሁሌ ተገዛን። ከፊሉ መገበያያችን ላይ ምስሉን አተመ፤ ከፊሉም የወዳጆቻንን ጀርባ ላይ ጽሁፉን። እኝ ግን ተስፋ አልቆረጥንም፤ ኖርን። ሲያቆስሉን ስንጨክን፣
የጠዋቱ ነፋሻማ አየር የመኝታ ቤቴን መስኮት መከፈት ተጠቅሞ፣ ክፍሉን በቅዝቃዜ አውዶታል። ተከናንቤ የተኛሁት ጨርቅ እግሮቼን እንዳልሸፈናቸው የታወቀኝ የሰውነቴ ክፍሎች መሆናቸው እስኪዘነጋኝ ድረስ ብርዱ የጠዘጠዘኝ ጊዜ ነበር። ነቃሁ። መንቃቴን እርግጠኛ ባልሆንም፣ ነቃሁ። ፈጠን አልኩና በድን የሆኑት እግሮቼን በእጆቼ እርዳታ ወደ ውስጥ ሰበሰብኳቸው። መልካም ስሜት ነበር። እንዲህ ሞቅ ብሎ፣
ምሬት ተሰምቷችሁ፣ ሁሉም ነገረ እሬት፣ እሬት ያላችሁ ጊዜ አለ? ናላችሁ በሆነ ምክንያት 180 ዲግሪ ዞሮ፣ ማንባረቅ፣ ማንባረቅ አሰኝቷችሁ ያውቃል? ከፈሳችሁ ጋር ሳይቀር መጣላት፣ መጣላት ከጅሏችሁ ያውቃል? መጮህ፣ መጮህ፤ ማበድ፣ ማበድ ብሏችሁ ያውቃል? አንዳንዶቻችን በተለይ ለዚሁ እንቆቅልሽ መድኃኒት ፍለጋ ያልማስነው ጉድጓድ፣ ያልቆረጥነው ቅጠል፣ ያላቋረጥነው
ከፍተኛ፦ ዜሮ ዜሮ ቀበሌ፦ ዜሮ ዜሮ የቤት ቁጥር፦ ዜሮ ዜሮ አመልካች፣ እኔ ጭላሎ በረደድ፣ የእነ ጩኒ አባት ስሆን፤ የማመለክተው ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል። ያስቸገረኝ ወጠጤ ጎረምሳ ስሙ ጥጋቤ ገላግሌ ነው። ጥጋቤ ገላግሌ አጠበዳደሉ ዝሆን ነው የሚያክለው፤ ሳር አይበላም እንጂ፣ ሲፈጥረው በሬ ነው። አንድ ቀን፣ የህዳር ሚካኤልን ጠላ
ከረጅም እረፍት በኋላ ተመልሰናል።
Not following anyone at the moment.